ETHIO ORANGE COUNTY EDER
ኢትዮ ኦሬንጅ ካውንቲ እድር

It is a long standing Ethiopians' tradition to help one another financially as well as emotionally when a person loses a family member. This self-organized and self-managed organization is called Edir. Ethiopians in the Orange County California area formed our own Edir and called it Ethio Orange County Edir which started providing service since 1995 and was recognized legally in 2018. This Edir was established in accordance with California state law and its address is in the City of Anaheim California. In addition to providing financial assistance, Ethio Orange County Edir also assists the bereaved with other forms of assistance during the mourning period such as providing food, refreshments and helping with various tasks and providing emotional support to the family. The Ethio OC Edir members elect 7 board members who will serve for 2 years. The board meets periodically to discuss issues related to the Edir and to coordinate assistance when a member is impacted.

በሃገራችን ባህል መሠረት እድር ለዘመናት ሃዘንተኞችን ሲረዳ እና ሲያጽናና የቆየ ባህላዊ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል። እኛም በአሜሪካ ኦሬንጅ ካውንቲ ካሊፍርንያ ነዋሪዎች የሆንን ኢትዮጵያውያን የአገራችንን ባህል በመከተል እርስ በእርሳችን ለመረዳዳት እንድንችል የራሳችንን እድር አቋቁመናል። ይህ ስሙ ኢትዮ ኦሬንጅ ካውንቲ እድር ተብሎ የሚታወቀው እድር የተቋቋመው እና ለአባላት አገልግሎት መስጠት የጀመረው እንደ አውሮፓ ቀን አቆጣጠር 1995 ቢሆንም ፤ በአውሮፓ ቀን አቆጣጠር በ 2018 በካሊፎርንያ ግዛት ህጋዊ ሆኖ ተመዝግቧል። የዚህ እድር ቢሮ አናሃይም በሚባለው ከተማ ነው። እድሩ የሚመራውም በጠቅላላ አባሎች በተደነገገው እና በጸደቀው ህግ መሰረት እና በየሁለት አመቱ በሚመረጡ ሰባት የቦርድ አባሎች ነው። እድሩ ከሚሰጡት አገልግሎቶች መካከል አባሎች ለቅሶ ሲረዱ ለአባላት ወይም አባሎች ላስመዘገቧቸው ተተኪዎች የገንዘብ ክፍያ ማድረግ ፤ ለሃዘን ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ ምግብ መጠጥ እንዲሁም አንዳንድ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ፤ የሟች ቤተሰቦችን ማፅናናት እና ሌሎች አስፈላጊ መስለው የሚገኙ ነገሮችን ማድረግ ነው።